zare yhun nege
• Written by user674124250
ዛሬ ይሁን ነገ ሞቴን አላቀው
ላዝን ልዘምር እንጂ ቀኔን ቀን ያውጣው
ሐዘን ትካዜ ጭንቀት ውስጤ ለገባው
የሌላውን እንጃ የኔን በዜማ ላውጣው
አዩኝ አዩኝና ኩነኔ ነው አሉ
የኔ ዜማ ማዜም ግርም ያለው ሁሉ
ባያቁት ነው እንጂ ባይገባቸው ውሉ
ዜማዬ ያሬድ ነው መሀሌቴ ሁሉ
እዚ ብቻ አደለ ከተማው በሙሉ
ሲሰማ ሲነገር ምነው ጉድ ማይሉ
ምን አሻማ አንዳንዴ ይዘፈናል አሉ
ሲወለድ አያቀው ሲሞትም አያቀው
የቀን የቀኗ ላይ እንዲህ የሚኖረው
ምን አጣው ብሎ ነው ሰዉ ሚጨነቀው
አደግዳጊው ብዙ በየሰዉ ቤት
ይሄን ቤት ከዚያ ቤት የሚያነካኩት
ምን አገኝ ብለው ነው ከዳ ሚገቡት
እኔስ ይሻለኛል ከሰዉ ጭቅጭቅ
በፈገግታ መኖር ከዜማዬ ሳርቅ